Skip to content

vacancy(የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ)

    የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ
    ብሄራዊ ግልጽ (ጨረታ ማስታወቂያ

    በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ማለትም የውሃ ታንከር (Reservoir) ግንባታ፤ የግፊት መስመር እንዲሁም የኤሌክትሪክ መካኒካል ሥራ ለማሠራት በመጠጥ ውሃ ግንባታ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ እና የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

    ስስሆነም በሥራው ስመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ፤
    በውሃ ግንባታ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና WC/ ደረጃቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
    ለሥራው የመጠጥ ውሃ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ አግባብነት ያለው ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና TN ያላቸው፤ ቢያንስ h3(ሦስት) አመት በላይ በዘርፉ የሥራ ልምድ ያላቸው፡፡

    . የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዥ| ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 21(ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ::

    ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴhኒካል እና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻው በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ንብ/ስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሃያ ሁለተኛው ቀን |22ኛው/ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሥራ የጨረታ ሰነድ ይከፈታል ፡፡

    ጨረታው በሃያ ሁለተኛው ቀን (22ኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡

    22ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡

    ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 250,000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይንም በተረጋገጠ በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው ::

    የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርበታል ፡፡


    . መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

    ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ ፡፡

    በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና
    መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender