Skip to content

invitation to bids by addis ababa city administration design and construction works

  በግልፅ የወጣ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
  የጨረታ ቁጥር አ/ከ/ክ/ከ/ዲ/ግ/ስ/ፅ/ቤ/ም/ቡ/015/2016


  በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በወረዳ ዐላ ለሚያሰራው የአድሳት ስራ በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሎትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡


  ተ.ቁ. :- 1
  የስራው ዓይነት :- የወዳ 4 ኢንደስትሪያል ኮሌጅ 3 ጂ+2 ህንፃ እድሳት፣ ላይብረሪ እና ወርክሾፖች እድሳት
  የግንባታ ጊዜ :- 90 ቀን
  ደረጃ (በቀን) :- GC-4|BC-3 እና በላይ
  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን :- 500,000
  የጨረታ ሰነድ የሚገዛበት ቀን :- 16ተኛው የስራ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  የጨረታ መክፈቻ ቀን :- 16ተኛው የስራ ቀን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  ምርመራ :-


  1. ለሥራው ሀጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የ2016 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የ2ዐ16 ፈቃድ ያደሱ ቢሆኑም ሁሉም ተጫራቾች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡ ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ206 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ሁለቱም፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (Supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መሊያ ቁጥር ያላቸው፡፡ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ስራ ላላቸው ስራ ተቋራጮች ደግሞ ያላቸው የግንባታ አፈፃፀም ከ75 ፐርሰንት በላይ መሆኑን የሚገልፅ መልካም አፈፃፀም (Good Performace) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ሁሉም ተወዳዳሪ ተቋራጮች ቀድሞ ለሰሩት ፐሮጀክት ከሰሩበት ተቋም የቅርብ ጊዜ የመልካም የስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

  2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት 5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በምህንድስና ግዢ ቡድን ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው ( Original) እና የማይመለስ ቅጂ(Copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000 አንድ ሺህ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው የቴከኒካል ሰነድ ባለው መስረት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክትእዘዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (uNCONDITIONAL BANK GUARANTEE ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው የብር መጠን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት (ADDIS KETEMA Sub City Design and Construction Works Office) ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ስነድ በጨረታው ሰነድ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ውድድሩ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴከኒካል አንድ ኦርጂናል እና ቴክኒካል
   ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BD SECURITY) ብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ላይ ፊርማና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸውን 6 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሦስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ እና ቴከኒካል ሰነድ ሦስቱን
   ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ሙሉ በሙሉ ባይገኙ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በግንባታ እና በዲዛይን በንኡስ ተቋራጭነት ለማሳተፍ የወጣውን መመሪያ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም የሚሳተፉበትን የስራ ዝርዝሮች በመጥቀስ ከስምምነት ደብዳቤ ጋር አያያዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ ስራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ
   ይችላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያ እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሰሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ስልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው በፈራሚው ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ባለሙያ ከአንድ ስራ ተቋራጭ በሳይ ፈርሞ ከተገኘ ያስፈረሙት ስራ ተቋራጮች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
  9. የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማከበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶች በሁሉም ገጾች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም
   ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የድርጅቱ የስራ ልምድ እና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁ ዶክመንቶችን አሰሪ መስሪያ ቤት ኦሪጅናል ዶከመንት የመጠየቅ እና ዶከመንቶቹን ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 827 9324 መረዳት ይቻላል፡፡
  12. ስድራሻ፡- መድኃኔዓለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ ራስ ኃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎን የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን 4ኛ ወለል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ
   መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

   የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

  Read more Construction Tenders

  https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

  http://constructionproxy.com/category/tender