Skip to content

INVITATION TO BID BY THE National Lottery Administration

    ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
    የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

    የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2016 በጀት ዓመት በድሬዳዋ ከተማ B+G+3 ሕንፃ /B+G+3 Mixed use Building/ ኮንትራክተሮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን በማሟላት የሚሰሩ ኮንትራክተሮች ደረጃቸው GC-5/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
    ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታታሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/በመክፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ያለባቸው ብር 500.000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር/ በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ t/Unconditional Bank Guarantee from Recognized Bank of Ethiopia/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
    ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለጹትን የቴክኒካል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋናና እና ሁለት ኮፒ ለየብቻው እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ የያዘ አንድ ዋናና ሁለት ኮፒ ለየብቻው እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
    ጨረታው ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና መ/ ቤት ይከፈታል፡፡
    አስተዳደሩ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር o1-1267816 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
    የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

    የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

    አዲስ ዘመን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender