ethio telecom
ኢትዮ ቴሴኮም
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በቢሾፍቱ ከተማ የቢሾፍቱ 2 ሽያጭ ማዕከል ፓርቲሽን ስራ (Shop Partition work) ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ መለያ ቁጥር RFO፦ 4239688 በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መስፈርት፡-
- ጨረታው ከኀዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ☞ የባንክ ሲፒኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
- 6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-09-94/ 022-112-16-60 ደውስው መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
Read more Construction Tenders
https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders