Skip to content

INVITATION TO BID BY THE ETHIO TELECOM

    ethio telecom የጨረታ ማስታወቂያ

    ethio telecom የጨረታ ማስታወቂያ ኢትዮ ቴሲኮy ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በቢሾፍቱ ከተማ የቢሾፍቱ 2 ሽያጭ ማዕከል ፓርቲሽን ስራ (Shop Partition work) ሥራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ መለያ ቁጥር REQ፦ 4239688 በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ሕጋዊ የታደሠ ፈቃድ ያላችሁና ቢያንስ አንድ አመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

    መስፈርቶች፤
    1. ጨረታው ከኅዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
    2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
    3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
    4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 15,000.00/አስራ አምስት ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
    5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
    6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
    7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል:: 8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-11-0994 / 022-112-660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender