የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር አአከመባ ግብዓት/0-1/012/2016
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2016 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ አስፋልት ሚከስ ለማምረት ከታች የተገለፀውን የአስፋልት ፕላንት ማሽንለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በሰዓት የኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ
በሰዓት ለኪራይ የተፈለገ የማሽነሪ ዓይነት – የአስፋልት ፕላንት ማሽን ኪራይ አገልግሎት
ብዛት በቁጥር – 1
የጨረታ መለያ ቁጥር – አአአ ባ ግብዓት /n–1/012/2016
ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበ ት ጊዜ – 60 ቀን
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት – ህዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት – ህዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡15
የጨረታ ማስከበሪያ በብር – 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር
ስለዚህ፤
1, ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደስ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ሰርትፍኬት እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች ለአስፈልት ፕላቱ ለሚወዳደሩበት ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብራ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ (ሊብሬ) ህጋዊ ውክልና እንዲሁም አስፋልት ሚክስ ለማምረት ከሚመለከተው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣነ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ
ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡ - ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋስትናው ከታወቀ ባንክ በባንክ ጋራንቲ ወይም በCertified Payment Order (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- 5. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1ዐ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
(ሳርቤት ፐሽኪን አደባባይ አጠገብ)
MAH #TC 011-3-71-41-03 /011-3-72-28-15
Read more Construction Tenders
https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders