Skip to content

INVITATION FOR BID BY THE Gedeo Zone

    የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
    በደ/ኢ/ብ/ብ/ሕ/ከ/መንግሥት የጌዴኦ ዞን የራጴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት የራሴ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ ቤት በቁጥር ራ/ወ/አ/ጽ/ቤት 2659/16 ዓ.ም በ26/2/2016 ዓ.ም በጻፈልን ደብዳቤ መሠረት የአስተዳደር ቢሮ G+1 ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። በዚሁም መሠረት ተጫራቾች፡-

    1. BC/GC level 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
    2. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2016 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣
    3. 3. ከመንግሥት የሚፈለግበትን የዘመኑን የግብር እና ታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ በበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከክልሉ ታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል፣
    4. ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት እንደተጠበቀ ሆኖ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮችን እየጋበዘ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናልና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ በመያዝ በፕሮጀክቱ ስም በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
    • ተቋራጮች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ
      አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ሰነድ /በፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ የተደረገ/ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ሃያ አንድ ቀናት/ ቆይቶ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በጌዴኦ ዞን ራኤ ወረዳ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
    • በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርበታል። * እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና (unconditional) ማቅረብ ይኖርበታል፤ በጥሬ ገንዘብ /በኢንሹራንስ/በሌላ ማቅረብ አይቻልም።
    • በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያስደርጋል።
      ጨረታው በውክልና የሚመጡትን አይመለከትም።
      ጨረታው የሚዘጋው በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ከፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰአት በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ይሆናል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
      · የቦታ ጉብኝት (Site Visit) ከአሰሪ መ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
    • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟሉ የሚቀርቡ የሥራ ተቋራጮች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ።
    • ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ጨረታውን አሸንፈው ሥራውን ያቋረጡና ሥራውን ያጉላሉ በጨረታው አይሳተፉም፡፡
      ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
      አድራሻ፡- የጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0948911976/ 0916378090
      የጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender