Skip to content

INVITATION FOR BID(የዲዛይን ስራ አገልግሎት ብሄራዊ)

    የዲዛይን ስራ አገልግሎት ብሄራዊ
    ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

    በአብከመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተልማት ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት ለሚያሰራው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች የሚሆን የዲዛይን ዝግጅት ስራ ማለትም፡-

    ሎት 1 ጌጠኛ መንገድ ፤የግሪን ኤሪያ አጥር እና በቴራዞን የማስዋብ ስራ ፤ የድጋፍ ግንብ ስራ ፤የቄራ አጥር እና ሴፍቲ ታንክ ስራ፤ የተፋሰስ እና የመሸጋሪያ ድልድይ ዲዛይን ስራ
    ሎት-2 የከተማ አቀፍ የተፋሰስ ኔት-ወርክ (መስመር) ፕላን አገልግሎት ስራ ለማሰራት በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች /አማካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

    ስለሆነም በሥራው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡
    በጠቅላላ ስራዎች አማካሪ ድርጅቶች ደረጃቸዉ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
    ለስራው በማማከር ስራ ህጋዊ አግባብነት ያለዉ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ! የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው/የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና TIN ያላቸው፤ቢያንስ ከ3 (ሶስት) አመት በላይ በዘርፉ የስራ ልምድ ያላቸው።

    የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ ኣስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ (ሎት) የማይመለስ የኢትዮ. ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

    ተጫራቾች በየሎቱ ለየብቻው የጨረታው የፋይናንሽያል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሃያ ሁለተኛዉ ቀን /22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባ ይችላሉ።
    በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ ፡4:30 ሰዓት ላይ ከላይ የተዘረዘሩትን የዲዛይን ዝግጅት አገልግሎት ስራ የጨረታ ሰነድ ይከፈታል።

    ጨረታው በሃያ ሁለተኛዉ ቀን (22ኛ)ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 22ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።

    6.ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 እና ለሎት 2 ለእያንዳንዳቸዉ ብር 13,000 (አስራ ሶስት ሽህ) ብር በጥሬ ገንዘብ ወይንም በተረጋገጠ በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

    የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

    መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም
    በስልክ ቁጥር፡- 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

    በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender