Skip to content

INVITATION FOR BID(የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

    የጨረታ ማስታወቂያ

    1.የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰመራ ኤርፖርት ኤርፊልድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የማማከር አገልግሎት፣ ዲዛይን ግምገማና ማፅደቅ፣ ኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና ኮንትራት አስተዳደር ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን ለመጋበዝ ይፈልጋል።

    1. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰመራ ኤርፖርት ኤርፊልድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዲዛይን ግምገማ እና ማፅደቅ፣ ኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና ግንባታ ውለታ ማስተዳደር።

    2.አማካሪዎች በአገር ውስጥ በኢትዮጰያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን የተመዘገቡ፣ ለማማከር አገልግሎት የ2015 ዓ.ም. የሚያገለግል ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

    3.ፕሮጀክቱ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ይገኛል።

    4. ለጨረታ የሚቀርቡት የማማከር አገልግሎት አጠቃላይ መግለጫ የሚከተለው ነው።

    ዝርዝር የዲዛይን ግምገማዎችን ማድረግ እና ዲዛይኖችን ማፅደቅ፤
    የሥራውን ጥራት መቆጣጠር እና የግንባታ ውል ማስተዳደር፤

    5.የፕሮጀክቱ ጊዜ 365 ቀናት ነው፤

    6.ጨረታው የሚካሄደው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት እና ለሁሉም ተወዳዳሪ ተጫራቾች ክፍት በሆነ ውድድር መንገድ ነው።

    7. የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል አቅርቦት ሰነድ ዋናው እና ቅጂዎች በተለየ ኤንቨሎፕ ታሽገው “ኦሪጅናል” ሰነድ እና “ኮፒ” የሚል ምልክት ይደረግባቸዋል። የጨረታ ሰነዱ ገፆች በሙሉ ታሽገው በተጫራቾች መፈረም አለባቸው።

    8. በስራ ጨረታ ላይ ከሚሳተፉ የዲዛይን-ግንባታ ተቋራጮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት (Mou) ያላቸው ተጫራቾች በፕሮጀክቱ ላይ አይሳታፉም።

    9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ኤንቨሎፕ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

    10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

    11.የታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን-ቴከኒካል ክፍል ኅዳር 27/2015 ዓ.ም. እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከቀኑ 9፡00 በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ውድቅ ይሆናሉ።

    12. የታሸገውን የጨረታ ዶክመንት በተለያየ ኤንቨሎፕ ማለትም (ቴክኒካል ፕሮፖዛል፣ የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል እና የጨረታ ማስከበሪያ) እና ፖስታ ኢንቨሎፖችን በውጪ በኩል በትክክል “ORIGINAL” እና “COPlES” የሚል ጽሁፍ በመፃፍ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ማክሰኞ ኅዳር 27/ 2015 ከሰዓት በሀዋላ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ 9፡30 በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መ/ቤት የሰራተኛ ዋና ካፌቴሪያ ውስጥ ይከፈታል።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

    የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T 344

    ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

    ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

    ስልክ ቁጥር፡_ 011-517-4918

    ኢ-ሜይል: assefah@ethiopianairlines.com

    አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender