Skip to content

INVITATION FOR BID(የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት)

    የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት

    የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት በ2015 ዓ.ም. ለሚያሰራው የG+2 ህንጻ የግንባታ የቁጥጥር ስራ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውን የአርቴክቸራል እና ኢንጅነሪንግ አማካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

    ተ/ቁ
    የስራው አይነት
    ደረጃቸው
    የማጠናቀቂያ ግዜ የመቁጠሪያ ቀናት
    ቢድ ቦንድ በሲፒኦ ቼክ እና ካሽ

    1.በባህር ዳር እና ጅጅጋ የግንባታ ቁጥጥር ስራ
    ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
    240 ቀናት
    50,000.00

    2.በአሶሳ እና ጅማ የግንባታ ቁጥጥር ስራ
    ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
    240 ቀናት
    50,000.00

    3.በጋምቤላ የግንባታ ቁጥጥር ስራ
    ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
    240 ቀናት
    25,000.00
    ኢንስቲትዩታችን ይህን የግንባታ ቁጥጥር ስራ የሚፈጽመው በማስታወቂያውና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከሚያሟሉት መሀከል በመምረጥ ይሆናል።

    ተጫራቹ የሥራ ብቃታቸውንና ውጤታማነታቸውን ባለፉት 5 ዓመታት ያለምንም እንከን የተወጡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ከአሰሪው መስሪያ ቤት እና ከሌሎች መንግስታዊ ቢሮዎች የሥራ ማስጠንቀቂያ ያልደረሳቸው መሆን ይኖርበታል።

    ተጫራቹ በውጭ ኦዲተር የተረጋገጠ የፋይናንስ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል/ይኖርበታል።

    ተጫራቾች ካለፋት 5 ዓመት ውስጥ የሥራ አፈጻጸም ማስረጃቸውን፣ በበጀቱ አመቱ የታደሰ ህጋዊ ፈቃዳቸውን እንዲሁም ከገቢዎች ባለስልጣን መ/ቤት ጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ፤ (ታክስ ክሊራንስ) ተ.እ.ታ የተመዘገበበት ሰርተፊኬት እና ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የሚሰጠውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት በበጀቱ አመቱ የታደሰ ዋናውን በማቅረብ በግዥ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ከሚገኘው መ/ቤታችን ከግዥ ኬዝ ቲም ሰነዳቸው ከተረጋገጠ በኋላ የማይመለስ ብር 400.00 ከፍሎ መውሰድ ይችላል።
    አንድ ተጫራች ከአንድ ጨረታ በላይ መወዳደር አይችልም።

    አንድ ተቋራጭ ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
    ተቋራጮች የዋጋ ማቅረቢያውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ በጨረታው የስራ ዝርዝር ላይ በተገለጸው መሰረት ለሚያሠሯቸው ስራዎች አጠናቆ ለመስራት የሚሰጡትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ በግልጽ በሚነበብ መልኩ መጻፍ አለበት።

    ተቋራጮች የጨረታ ሰነዶችን ሞልተው ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ኦሪጅናል እና ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ሁሉንም ለየብቻ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት ኤንቨሎፖች ላይ በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማረጋገጥ በተጨማሪ ሙሉ አድራሻቸውን በመጻፍ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

    ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

    መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ማሳሰቢያ፦ በገዙት ኦርጅናል ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ፈርመው ማህተም በማድርግ ሙሉ ሰነዱን ይመልሱ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ በተገለጸው መጠን በድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር 1000007241295 በድርጅታችሁ ስም አስገብታችሁ የባንh አድቫይስ ይዘው በመምጣት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

    ፖ.ሳ.ቁ 1090 ስ.ቁ 011 551 2299
    ወይም 011 558 6313/ አዲስ አበባ
    የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender