August 26/2025
የጨረታ ማስታወቂያ
EEU/PPM/05/2018(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ለካራ ቆሬ ዕቃ ግምጃ ቤት የአጥር ግንባታ የእጅ ስራ በዘርፉ ከተሰማሩ ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው îየታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ክወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በእ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥርEEU/PPM/05/2018(NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስክቀነ- 8.00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከ ቀነ- 8.30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በ ስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 12:00-6:00 ከ ሰዓት 7፡00 -11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6:00 መመልከት ይቻላል ፡፡
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111263153 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
Read more Construction Tenders
https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders