የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአዲስ አበባ ቴክኖሎጅ እንስቲትዩት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በትብብር የሚያካሂደው የሲቪል ምህንድስና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አካል በሆነውና በያዝነው 2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚያስቀጥለው ፕሮግራም መመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ERA Supposed Civil Engineering Post Graduate Program at Addis Ababa University (AAiT) follow the announcement carefully.

        የትምህርት ዓይነቶች፤

  1. ሃይድሮሊክስ ምህንድስና
  2. ስትራክቸራል ምህንድስና
  3. ጆኦቴክኒካል ምህንድስና

     የመመዝገቢያ መስፈርት፡

በሲቪል፤ በሃይድሮሊክስ፤ በኮንስትራክሽን፤ በመስኖ፤ በውሃ ምህንድስና እና ተዛማጅ ሙያ ከታወቀ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ፎቶ ኮፒ በምዝገባ ወቅት ማቅረብ የሚችሉ፤

እና

ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የመግቢያ ፈተናው ቀንና ሰዓት ወደፊት ይገለፃል፡፡

ለመመዝገብ አስፈላጊ ሁኔታዎች፡

  1. ድግሪና የትራነስክሪፕት ዋና ኮፒና 1 ፎቶ ኮፒ
  2. አንድ የፓስፓርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
  3. ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ፤ አንዱ አሁን ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት መሆን አለበት
  4. የመመዝገቢያ 80 ብር ብቻ፡

ከአጠቃላይ የትምህርት ክፍያ 5% 3 235.85 (ሶስት ሽህ ሰላሳ አምስት ብር) በተማሪው የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋና ርጅስተራል (6 ኪሎ)

የምዝገባ ቀንና ሰዓት፡-

ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ፤ ሀሙት የካቲት 9 2009 ዓ.ም (ለተከታታይ ሶስት ቀናት)

ga('create', 'UA-92778134-1', 'auto'); ga('send', 'pageview');