የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት - መቐለ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በትብብር የሚያካሂደው የሲቪል ምህንድስና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አካል በሆነውና በያዝነው 2008 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚያስቀጥለው ፕሮግራም መመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

        የትምህርት ዓይነቶች፤

  1. ሃይድሮሊክስ ምህንድስና
  2. ስትራክቸራል ምህንድስና
  3. መንገድና ትራንስፖርት ምህንድስና
  4. ጆኦቴክኒካል ምህንድስና

     የመመዝገቢያ መስፈርት፡

  1. በሲቪል፤ በሃይድሮሊክስ፤ በኮንስትራክሽን፤ በመስኖ፤ በውሃ ምህንድስና እና ተዛማጅ ሙያ ከታወቀ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ፎቶ ኮፒ በምዝገባ ወቅት ማቅረብ የሚችሉ፤

እና

  1. ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የመግቢያ ፈተናው ቀንና ሰዓት ወደፊት ይገለፃል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ፡

በአዲስ አበባና አካባቢው የሚገኙ አመልካቾች በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 804

የምዝገባ ቀንና ሰዓት፡-

ቅዳሜ መስከረም 22 ቀን 2008 ዓ.ም ፤ ቅዳሜ መስከረም 29 እና ቅዳሜ ጥቅምት 6 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ

3፡00 ሠዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ፡

Tags: Ethiopian Roads Authority,, MSC,, Mekele,

ga('create', 'UA-92778134-1', 'auto'); ga('send', 'pageview');