Skip to content

የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ ለመከራየት በክፍት ጨረታ  ስለመጋበዝ

    September 3/2025

      Bid Announcement No. የጨረታ መለያ ቁጥር ኢ.ኢ.ኮ/ኮንስትራ/ወጪ/3461/2017

    አዲስ አበባ

    ጉዳዩ፡ የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ ለመከራየት በክፍት ጨረታ  ስለመጋበዝ፡፡

    የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኮንስትራክሽን ዘርፍ ለአዲማ አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ለአዲስ አበባ፣ ሃረር መንገ ፕሮጀአገልግሎት የሚውሉ ከ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ዴርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።

    1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ’ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ’ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

     2. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የግዥ አፈፃፀም ሕጎች እና የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን-ኮንስትራክሽን የግዥ መመሪያ በተገለጸው የክፍት ጨረታ ሥነ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ይሆናል።

    3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00( አስር ሺህ) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ (Unconditional Bank Guarantee) የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኮንስትራክሽን ዘርፍ) ማሰራት  አለባቸው።

    4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሄራርድ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ ወይም ከስር በተቀመጠው ሊንክ በመጠቀም መውሰድ ይችላሉ፡፡

    5. የዕቃው ዝርዝር እና አገልግሎቶቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (specification)ተያይዟል።

    6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡

    7.ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቢያንስ ሶስት  ወር የሚጸና መሆን አለበት፡፡

    8. ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ ማዘጋጀትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

    9. ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ መስከረም 12 ቀን 2018ዓ.ም. ከጥዋቱ 4፡30ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡

    10.ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡

    11. ጨረታው የቴክኒክ ስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል

    12. መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

       አድራሻ፡-

    የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ኮንስትራክሽን ዘርፍ (ኢ.ኢ.ኮ/ኮንስትራ) ሕንጻ 1 ሶስተኛ ፎቅ ፡  የግዥ ቡድን ቢሮ

    የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል  ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251-960-041-951/+251-911-153-389/+251-934-932-921  አዲስ አበባ 

    https://forms.office.com/r/NYhvYi9Pw8

    
    For more information: Address:
     https://forms.office.com/r/NYhvYi9Pw8

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender